እውነትነቱን በመስቀል ላይ
መቶ አለቃው ጌታዬን ቢያይ
ተንበረከከ ሰገደለት
ያውቃል የጌታን ቅንነት
እንኳን አሁን ከፍ ከፍ ብሎ
አሸንፎል ጥንትም ጥሎ
ሳያስፈራራ ሰው አንበርካኪ
እንደእርሱ የለም ፍቅር ሰባኪ
አዝ፡(፬)
አቤት ደግነት ቸርነቱ ለሰው ያሳው ምህረቱ
አቤት ደግነት ቸርነቱ ለሰው ያሳው ምህረቱ
ፍቅር ምህረቱን የቀመሱቱ
ውበቱን ያዩ ሐዋሪያቱ
ስለእርሱ ኖረው ለበጎ መሞት
ለፍቅሩ ሆኑ ሰመኃታት
ተነክተው በምህረቱ
ተነክተው በቸርነቱ
ነክቶአቸው ገርነቱ
ነክቶአቸው የዋህነቱ
የቱ ጀግና ነው እጁን ያልሰጠ
ኢየሱስን አይቶ ያልደነገጠ
ልከተለህ ያላለህ ማነው
የኢየሱስ ፍቅር አሸናፊ ነው
ከጫፍ ጫፍ ስንቱን ማረከ
በፍቅሩ አንበረከከ
ምን ዓይነት ፍቅር ነው እንጃ
ወደደንው ያለ ጠመንጃ
ከጫፍ ጫፍ ስንቱን ማረከ
በፍቅሩ አንበረከከ
ምን ዓይነት ፍቅር ነው እንጃ
ሰገድን ያለ ጠመንጃ
አዝ፡
አቤት ትህትና አይ ቅንነት
ሰውን ያስተማረ ኑሮ በህይወት
የሚሸጠውን እግር ያጠበ
እሩሩ ነው ጌታ ፍቅርን ያነገበ
ይህንን ጌታ የምትወዱት
አስቲ ከእኔ ጋር ኢየሱስን እንደዚህ በሉት
ይህንን ጌታ የምትወዱት
አስቲ ከእኔ ጋር ኢየሱስን እንደዚህ በሉት
(፬)
እንዳንተ ያለ እንዳንተ ያለ
እንዳንተ ያለ ኸረ ማን አለ
እንዳንተ ያለ ኸረ ማን አለ
እንዳንተ ያለ ኸረ ማን አለ
Lyrics Submitted by Eskedar Abebe
Lyrics provided by https://damnlyrics.com/