Yelielegnen Keyet Lamta

Ephrem Tamiru

አልገባኝም በቤቴ ባንቺ ስለኮራሁ
ይህን ያህል ምን ጥፋት በሰው እንደሰራሁ
ሰው አልነካሁ አጥፍቼ አልተፈረደብኝ
ለምን ይሆን እኔ ሳልፈልግ ሰው የሚደርስብኝ

ሰው በቃኝ እስከምል ባንቺ ታምቻለው
ከማልጠብቀው ሰው ብዙ ሰምቻለው
ምን እንዳስከፋቸው ባይገባኝም እኔ
ባቋሜ አላዝንም ራሴን በመሆኔ

ዳሩ ደስ የሚለኝ ሰው ባይረዳኝም
አንቺ ታውቂኛለሽ ሀዘን አይጎዳኝም
ለሰው ደስ እንዲለው ለሌላው አልኖርም
ራሴን ድንገት ክጄ ወደኋላ እልልም

ምኑ ላይ እንደሆነ አልገባኝም ጥፋቴ
ለመውደድ በሞከርኩኝ እንደራሴ እንደቤቴ
ለምን ሰው እንዳስመሳይ ያስረኛል እንድቀጣ
በቃ ራሴ ነኝ እኔ የሌለኝን ከየት ላምጣ

አልገባኝም በቤቴ ባንቺ ስለኮራሁ
ይህን ያህል ምን ጥፋት በሰው እንደሰራሁ
ሰው አልነካው አጥፍቼ አልተፈረደብኝ
ለምን ይሆን እኔ ሳልፈልግ ሰው የሚደርስብኝ

ቅንነት ያደለው ዋሽቶ ያፋቅራል
ሰው ሊጥል አንዳንዱ ጉድጓድ ሲምስ ያድራል
ከቆፈሩት ጉድጓድ አምላክ በየጊዜው
አሻግሮን አልፈናል ጠብቆን በዘዴው

ምን እንድሚያገኙ በረካሁ አውቄ
ከሰው በታች ብሆን ዝንት አለም ወድቄ
ዳሩ ፈጣሪ አምላክ እንደሰው አይደለም
ይህው በሱ ድጋፍ የጎደለኝ የለም

ምኑ ላይ እንደሆነ አልገባኝም ጥፋቴ
ለመውደድ በሞከርኩኝ እንደራሴ እንደቤቴ
ለምን ሰው እንዳስመሳይ ያስረኛል እንድቀጣ
በቃ ራሴ ነኝ እኔ የሌለኝን ከየት ላምጣ

Lyrics provided by https://damnlyrics.com/