damnlyrics.com

Nat Baro

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ

አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ

ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ

ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ

ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ

አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ

ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ

ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ጥቁሯ ወርቅ ቀጥ እንደ ሸምበቆ

አኳሆኗ በአታሞ ምት ረቆ

ፍቅር ሲሞቅ እሳት ነዶ ማታ

ውበት አየው ዳንኪራ ሲመታ

ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ

ናት የባሮ

ቶም ሰርታ በዣንጥላው ብረት

በጨረቃ ፍቅርን ያዜምንበት

የታንኳው ላይ የወንዙ ሽርሽር

እረፍት አጣው ትዝባለኝ ቁጥር

ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ

ናት የባሮ

ናትባሮ ናትባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት

የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት

ናትባሮ ናትባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ

የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ

መሸት ሲል ጀምበር አዘቅዝቆ

ቀዩን ሰማይ ውሃው አንፀባርቆ

እያየሁዋት በጨረቃ መብራት

አማረኝ የታንኳ ላይ እራት

ጉድ አረገኝ በውበት ሳር አስሮ

አየ ባሮ

ናትባሮ ናትባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት

የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት

ናትባሮ ናትባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ

የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ይሔልቤ የሆነብኝ ምነው

ሀሳቤ ሁሌ ከአዊሊ ነው

ልያት እንጂ ወይ ሔጄ ዳግመኛ

ባደርጋት የሁሌ ጓደኛ

አሳ ሆኖ ልኮኝ እንጀራዬ

ከአዲስ አበባው የትውልድ አምባዬ

ተመለስኩኝ በፍቅሯ ተይዤ

የሸገር ልጅ ባዶ ቅርጫት ይዤ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ናት ባሮ አሳ አጠምድ ብሎ

ናት ባሮ ዘርግቶት መረቡን

ናት ባሮ እንዴት ለቆንጆ ሴት

ናት ባሮ ሰው ይጥላል ልቡን

ናት ባሮ አይኔእሷ ላይ ቀርቶ

ናት ባሮ አሳ አጣሁ ለእራቴ

ናት ባሮ ባዶ ቅርጫት ይዤ

ናት ባሮ ተመለስኩኝ ቤቴ

ናትባሮ ናትባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት

የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት

ናትባሮ ናትባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ

የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

ኚላል ባድ ኦፔኖ

Lyrics Submitted by Yosef alfaromeo

Enjoy the lyrics !!!